ለጥቆማ ሰጪዎቹ ማንነት ጥበቃ ይደረጋል?
የጥቆማ መስጫ ቅጹ ሚስጥራዊና ስም አልባ ነው። የጥቆማ ሰጪዎችን ማንነትና ሚስጥራዊነትን ለመጠበቅ ሲባል በቅጹ ውስጥ የሰዎችን ማንነት የሚገልጽ ጥያቄ አይካተትም። ቅጹ በሚሞላበትም ወቅት የጠቋሚዎችን ማንነት ሊለይ የሚችል መረጃ እንዳይካተት ጥንቃቄ እንዲደረግ ይጠየቃሉ።
የጥቆማ መስጫ ገጹን መጎብኝቴንና ቅጹን መሙላቴን የዓለም አቀፍ ስምምነት ተነሳሽነት (ዓስተ) ሰራተኞችን ጨምሮ የሚያውቅ ሰው ይኖራል?
የዓስተ ድረገጽ የጎብኚዎችን የኮምፑተር መለያ አድራሻ ይሰበስባል። የኮምፑተር መለያ አድራሻ በበይነመረብ ላይ ያሉ እቃዎችን የሚመዘግብ አድራሻቸውንም (ከተማና አገር) የሚገልጽ ልዩ መለያ ሆኖ ለበይነመረብ አገልግሎቱም የሚከፍልን አካል የሚያሳይ መረጃ ነው። ስለሆነም የምግብ ደህንነት ችግር ጥቆማውን የሚሰጡት በግል ከምፒውተርዎ ከሆነ የእርሶ ኮምፒውትር ለዚህ ተግባር ጥቅም ላይ መዋሉን ያሳይ ይሆናል፣ ግን ማን እንደተጠቀመበት አያመለክትም። ስለሆነም ለጥቆማ አሰጣጡ የግልዎን ኮምፒውተር አልያም ስለክ ባይጠቀሙና የጋራ የሆኑትን ከበይነመረብ ካፌዎች ተጠቅመው የጥቆማ መስጫ ገጹና ቅጹን መድረስ/መክፈት ቢችሉ ይመረጣል። በተጨማሪም በኮምፒውተሮም ላይ ሆነው የግል የርቀት ትስስር (Virtual private network (VPN)) መጠቀም ቢችሉ የተሻለ ሲሆን የግል የርቀት ትስስር ማለት በኮምፒውትሮ ላይ የሚጫን መተግበሪያ ሆኖ በይነመረብ ሲጠቀሙ አድራሻዎን ወደሌላ ቦታ በመቀየር በተሻለ ደህንነት ደረጃ ማንነቶ ሳይታወቅ እንዲቆዩ ያስችሎታል።
ቀጣሪዬ የጥቆማ መስጫ ደረገጹን መጎብኘቴንና የጥቆማ ቅጹን መሙላቴን ያውቃል?
የተወሰኑ ኩባንያዎች ከኮምፒውተሮቻቸው የትኛው የጥቆማ መስጫ ድረገጹን እንደጎበኘ ሊደርሱበትና ማንስ እንደሚጠቀምበት መለየት ይችሉ ይሆናል። ስለሆነም፣ የምግብ ደህንነት ችግሮችን ሲጠቁሙ ሊከተሏቸው የሚገቧቸው ዘዴዎችን እንደሚከተለው እናቀርብሎታለን፣ ይከታተሉ፤
- የመሥርያ ቤቶን/የቀጣሪ ኩባንያዎን ስልክ ወይም ኮምፒውተር አይጠቀሙ
- የመሥርያ ቤቶን/የቀጣሪዎን በይነመረብ አይጠቀሙ
- ደረገጹን በግልዎ ትር መደብ አለያም ማንነትን በማያሳውቅ incognito መስኮት ቢከፍቱ ድረገጹ በአሰሳ ታሪክ ተመዝግቦ እንዳይቀር ይረዳል።
- ለክሮም ማሰሻ በዊንዶውስ፣ በሊነክስ እና ክሮም ኦ ኤስ ከላይ በተጠቀሰው ዘዴ ለመጠቀም የሚከተሉትን፦ Ctrl + Shift + n በአንድ ላይ ይጫኑ፤ በማክ ድግሞ፦ ⌘ + Shift + n በአንድ ላይ ይጫኑ።
- ለፋየርፎክስ ማሰሻ በዊንዶውስ፣ በሊነክስ እና ክሮም ኦ ኤስ ከላይ በተተቀሰው ዘዴ ለመጠቀም የሚከተልውን፦ Ctrl + Shift + p ይጫኑ፤ በማክ ድግሞ፦ ⌘ + Shift + p ይጫኑ።
- ለሳፋሪ ፣ በማክ ድግሞ፦ ⌘ + Shift + n ይጫኑ።
- ለኢጅ በዊንዶውስ፣ በሊነክስ እና ክሮም ኦ ኤስ ከላይ በተጠቀሰው ዘዴ ለመጠቀም የሚከተልውን፦ Ctrl + Shift + p ይጫኑ፤ በማክ ድግሞ፦ ⌘ + Shift + n ይጫኑ።
ከላይ የተመለከቱትን ጥንቃቄዎች በትክክል ከተገበሩ የጥቆማ መስጫ ገጹን ማሰስዎንና ቅጹን መልተው መላክዎን ማንም በቀላሉ ሊያውቅ/ሊደርስበት አይችልም።
የጥቆማ መስጫ ቅጹ የበይነመረብ ኩኪዎችን ይጠቀማል? እኔንስ ሊለዩኝ/ሊያጋልጡኝ ይችላሉ?
ይሄ ደረገጽና የጥቆማ መስጫ ቅጹ ኩኪዎችን አይጠቀሙም።
እኔ ወደቅጹ የማስገባውን መረጃ በሶስተኛ ወገን ሊጠልፍ ይችላል?
መረጃ መጠለፍ የሚችለው ለአጭር ጊዜ ብቻ ሲሆን መረጃውን ወደኛ ሲልኩና ወደኛ ቋት ሲገባ የሙሉ ይዘቱ ድህንነት በHTTPS ሲለሚቆለፍ ጠላፊዎቹ በኮድ የተቀመጠውን ይዘት ወደ መደበኛ ቋንቋ መተርጎም አይቻላቸውም።
የጥቆማ ቅጹ ወደ ዓስተ ከተላከ/ከተላለፈ በኋላ ከትስስርና ከመለያ መረጃዎች ነጻ በሆነ በተለየና ለዚሁ ተግባር ብቻ በተዘጋጀ ቋት በአውሮፓ ህብረት ስልጣን ሥር እና በህብረቱ ህግጋት መሰረት ስለሚቀመጥ በዚህ ደረጃ መረጃው ከማንም ኮምፒውተር፣ ማንነትና የትስስር መረብ ጋር ያሚያያዝበት መንገድ የለም።
እኔ የሚልከው መረጃ እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?
ስም አልባው መረጃ ዓስተ በሚሰይማቸው ባለሙያዎች ተመርምሮ ይገመገማል። ባለሙያዎቹ በምግብ ደህንነት አደጋ ምክንያት እርምጃ መወሰድ አለበት የሚለ መደምደሚያ ላይ ከደረሱ ወደሚመለከተው አገር የምግብ ደህንነት ባለስልጣን አስቸኳይ የማንቂያ መረጃ ተልኮ የተጠቆመው ክስተት እንዲመረመር ይደረጋል።